"አዲስአበባ ዛሬም እንደ ወትሮወ ሁሉ የሰላም አየር እየተነፈሰች ፤ በሰላም ወዳዱ ህዝቧ ትብብርና አንድነት ሰላሟ ተጠብቆ፤ የቀን ውሎአቸውን እየከወኑ ነው ":-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

 

ዛሬ የ12 ኛ ክፍል የመልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና በመዲናችን አዲስአበባ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተጠናቅቋል ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከ36ሺህ 4ዐዐ በላይ የነገይቱ የከተማችን ብሎም የኢትዮጵያ ተስፋ የሆኑ ተማሪዎች በተለያዩ የመፈተኛ ጣቢያዎች የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተናቸውን ለተከታታይ ቀናት ወስደው በስኬት አጠናቀዋል ብለዋል።የፈተና አሰጣጥ ሂደቱ ስኬታማ እንዲሆን ያስቻላችሁ የፀጥታ አካላት ፤ መምህራንና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት የከበረ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ ያሉት ከንቲባዋ ከወዲሁ ለተፈታኝ ተማሪዎች መልካም ዕድል እመኛለሁ ብለዋል ።

Share this Post