" በፈተና ዉስጥ እያለፍን አንድነታችን ግን ከብረት እየጠነከረ ነው ፤አሁንም እንበረታ !እንፅና! " ከንቲባ አዳነች አቤቤ

 

ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያዊነቱን ነብርም ዥንጉርጉርነቱን ከቶ ሊለዉጥ አይቻለውም ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ማምሻውን ባስተላለፉት መልዕክት ገልፀዋል ።'በአራቱም የዓለም ክፍል የምትገኙ የኢትዮጵያ ልጆች አንዳንድ ምዕራባዉያን ሀገራት እና ሚዲያዎቻቸዉ ከሀገር ዉስጥ የእናት ጡት ነካሽ ባንዳዎች ጋር ሕብረት በመፍጠር ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተከፈተብንን የዉክልና ጦርነትና በቀደምቶቻችን ደምና አጥንት የቆመዉን የኢትዮጵያን ሉአላዊነትና ክብር የሚነካ ጣልቃ ገብነት ተቃዉማችሁ ከየትኛውም ጊዜ በላይ ከያላችሁበት ተሰባስባችሁ በአንድነት በአደባባይ ድምፃችሁን በማሰማታችሁ ኮርተንባችኃል ብለዋል።

በፈተና ዉስጥ እያለፍን አንድነታችን ግን ከብረት እየጠነከረ ነው ፤አሁንም እንበረታ !እንፅና! "ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር አብይ አህመድ እንዳሉት በፅናት በአንድነት ከቆምን በሩቅና በቅርብ ሀይሎች የተጋረጠብንን የህልውና ስጋት በአንድነት በማሸነፍ በድል አድራጊነት እንወጣዋለን " ። ከምንጊዜውም በላይ ህብረታችንን አጠናክረን እንቀጥል "ብለዋል።

Share this Post