ላለፉት ሶስት ቀናት ሲከናወን የነበረው የአመራር ግንባታ መድረክ ዛሬ ተጠናቀቀ።

 

በአዲስ አበባ ከተማ ባሉ ብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ላለፉት ሶስት ቀናት ሲከናወን የቆየው የአመራር የግንባታ መድረክ በዛሬው ዕለት ተጠናቋል ።

በአመራር ግንባታ መድረኩ ባለፉት የለውጥ ጊዜያት ባስተናገድናቸው ዋና ዋና ኩነቶች ያጋጠሙ ፈተናዎች ሀገር የማዳን የህልውና ዘመቻ የተሰጠው አመራር፤ እንዲሁም በቀጣይ በሚኖረን ተልዕኮ በምርጫ ያገኘነውን ሀገር የመምራት ዕድል፤ አኳያ የብልጽግና አመራር አሁናዊ ሁኔታ ግምገማ፤ በቅቶ የማብቃት ስትራቴጂ እና የብልጽግና ፓርቲ ጉዞና የወደፊት አቅጣጫ ዙሪያ ሰፊው ውይይት ተከናውኗል።የአመራሩ የአገልጋይነት መንፈስ ማጎልበት፣ የፓርቲን ስነ ምግባር ከማጠናከር አንጻር እንዲሁም ሀገራዊና ከተማ አቀፍ ተልዕኮዎችን በብቃት ከመወጣት አንጻር አመራሩ ያለበትን አሁናዊ ሁኔታ በመገምገም የነበሩ ክፍተቶችን በጥልቀት በመገምገም ያገኘነውን ዕድል በአግባቡ ተጠቅሞ መምራት የሚያስችል አቅጣጫ ተቀምጧል።

Share this Post