10
Dec
2021
የአዲስአበባ ከተማ ካቢኔ በሶማሌ ክልል በሚገኙ አካባቢዎች በዝናብ እጥረት ምክንያት ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን ለማቋቋም በማለም ያስተላለፈውን ዉሳኔ አስመልክቶ አቶ ሙስጠፌ ዑመር በቲዉተር አካዉንታቸዉ ለአስተዳደሩ ምስጋና አቅርበዋል ።
የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች በተፈጥሮ አደጋዎች ለችግር ለተጋለጡ ነዋሪዎች ማቋቋሚያ የሚሆን በድምሩ የ100 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል ።ከዉሳኔዎቹ መካከልም በሱማሌ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በዝናብ እጥረት ምክንያት በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች እየደረሰ ያለውን ጉዳት መነሻ በማድረግ ለክልሎቹ የአንድ መቶ ሚልየን ብር የአይነት ድጋፍ ውሳኔ አሳልፏል ፡፡ በዚህ መሰረት ለክልሎቹ በተናጠል የ50 ሚሊዮን ብር የአይነት ድጋፍ እንዲደረግ ተወስኗል ።
የከተማ አስተዳደሩን የወገን ደራሽነት ዉሳኔ አስመልክቶ የሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ሙስጠፌ ዑመር በማህበራዊ ትስስር ገፃቸዉ ለክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ለአስተዳደሩ የላቀ አክብሮት አለን ያሉ ሲሆን ስለተደረገው ድጋፍ በሶማሌ ክልል መንግስትና ህዝብ ስም ከልብ አመስግነዋል ።