የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአፋር ክልል ለሚገኙ የፀጥታ ሃይሎች የተለያዩ የምግብ አይነት ድጋፎችን አስረከበ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሸባሪው የህውኃት ቡድን በኢትዮጵያ አን...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአፋር ክልል ለሚገኙ የፀጥታ ሃይሎች የተለያዩ የምግብ አይነት ድጋፎችን አስረከበ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሸባሪው የህውኃት ቡድን በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የቃጣውን የሽብር ተግባር ለመመከት ከህብረተሰቡ ያሰባሰበውን የተለያዩ የምግብ ቁሳቁሶችን ለአፋር ክልል አስረክቧል፡፡ ባለፉት ቀናት በከፍተኛ የሀገር ፍቅር ስሜት ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን እና ለመላው የፀጥታ ሀይላችን ከተሰበሰበው ድጋፍ ለአማራ ክልል እና አፋር ክልል ለሚገኙ የጸጥታ ሃይሎች ከትላንት ጀምሮ በመሰራጨት ላይ እንደሚገኝ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል፡ የህልውና ዘመቻዉ በድል እስኪደመደም ድረስም የሚደረገዉ ድጋፍተጠናክሮ እንደሚቀጥል የተገለጹት ምክትል ከንቲባዋ የከተማችን ነዋሪዎችና ባለሀብቶች በከፍተኛ የሀገር ፍቅርና የደጀንነት ስሜት በአጭር ጊዜ ዉስጥ ላሰባሰባችሁት ከፍተኛ ድጋፍ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ ብለዋል፡፡

Share this Post