01
Nov
2021
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ከዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ተፈናቅለው በባሕርዳር ከተማ ዘንዘልማ ቀበሌ ተጠልለው ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የምግብና የአልባሳት ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፉን ያስረከቡት ከንቲባ አዳነች አቤቤአሸባሪው ህወሃት በአማራ እና በአፋር ክልል ህዝብ ላይ የፈፀመው መራር ግፍና በደል ታሪክ የማይረሳዉ በመላው ኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰ አሰቃቂ ተግባር ነው ብለዋል።ይህ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ኢትዮጵያን የማፈራረስ ከንቱ ምኞት አስፈፃሚ የሆነዉን አሸባሪውን የህወሃት ቡድን መላው ኢትዮጵያውያን በጋራ ተረባርበን በአጠረ ጊዜ መቅበር አለብን ብለዋል ።የአማራ ክልል ርእስ መሥተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ በበኩላቸው አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከዚህ በፊት በሽብር ቡድኑ ከተፈናቀሉ ወገኖች ጎን በመሆን አጋርነቱን አሳይቷል ብለዋል።ዛሬም ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና በማቅረብ ክልሉ ከሁሉም የጸጥታ ኃይሎችና ከሕዝቡ ጋር በመሆን አሸባሪ ቡድኑን ለመደምሰስ እየሠራ እንደሆነ ገልጸው ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ ሽብርተኛውን ቡድን ለመደምሰስ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።ድጋፉ ከአዲስ አበባ የሕብረት ስራ ማህበራት ኤጀንሲ ፣ከአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ኮርፖሬሽን እና ሌሎች የድጋፍ አሰባሳቢ የኮሚቴው አባላት ነው።