የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች የዕቅድ አፈጻጸም ውይይት ዛሬም ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው ። በትላንትናው ዕለት የተጀመረው የከተማ አስተዳደሩ የ2013 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀም...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች የዕቅድ አፈጻጸም ውይይት ዛሬም ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው ። በትላንትናው ዕለት የተጀመረው የከተማ አስተዳደሩ የ2013 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀም እና የ2014 ዓ.ም መሪ ዕቅድ ዙሪያ ከፍተኛ አመራሮች በቡድን ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛሉ ። በቡድን ውይይቱ ላይ በበጀት ዓመቱ የነበሩ ስኬቶች በቀጣይ አመት አጠናክሮ ለማስቀጠል እና የነበሩ ጉድለቶችን ደግሞ ለይቶ ለማረም በሚያስችል መልኩ እየተወያዩ ሲሆን በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተመሳሳይ ግንዛቤ እንዲኖራቸውም አመራሩ ሀሳቦችን እየተለዋወጡ ይገኛሉ።

Share this Post