18
Jul
2021
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች እና የፖሊስ አባላት በእንጦጦ በመገኘት "ኑ ኢትዮጵያን ፤አዲስ አበባን አረንጓዴ እናልብስ" በሚል መሪ ቃል በመካሄድ ላይ በሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐግብር ተሳትፈዋል ።
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፋንታ እንዳስታወቁት የፌደራል ፖሊስ የሀገር ሰላም እና የአካባቢን ፀጥታ ከመጠበቅ ባሻገር በተለያዩ የልማት ስራዎች በመሳተፍ የተጣለበትን ማህበራዊ ኃላፊነት በመወጣት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል ።
"ኑ ኢትዮጵያን እናልብስ "በሚለውን የአረንጓዴ አሻራ ሀገራዊ ጥሪን በመቀበል በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ችግኝ በመትከል ላይ እንገኛለን ብለዋል።