የዲፕሎማሲ ማዕከል በሆነችው ከተማችን ዓለም አቀፍ የቀዳማይ ልጅነት የልህቀት ስትራቴጅ ዓውደ-ጥናት አስጀምረናል::

የትውልድ ግንባታ ስራችን አካል የሆነው የቀዳማይ ልጅነት ልማት መርሀ ግብራችን” አዲስ አበባ ህፃናት ለማሳደግ የአፍሪካ ምርጥ ከተማ“ለማድረግ የልህቀት ማዕከል ተግባራዊ ማድረግን የሚመለከት ዓውደ ጥናት ነው።

በዓውደ ጥናቱ ላይ ሚንስትሮች ፣ የ11 አለም አቀፍ ፋውንዴሽን ስራ አስፈጻሚዎች ፣ ዩኒቨርስቲዎች ፣ የአፍሪካ ህብረት ፣ የተባበሩት መንግስታት ኤጀንሲ ተወካዮች እና የአለም ባንክ እንዲሁም በህጻናት ልማት ዙሪያ የሚሰሩ ተቋማት የተሳተፉ ሲሆን በመስኩ ጥናትና ምርምር ያካሄዱ ምሁራን የጥናት ወረቀቶቻቸውን በማቅረብ የቀረጽነውን ስትራተጂ ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችል ዕውቀት ፣ ልምድ እና ተጨማሪ አቅም የምናገኝበት መድረክ እንደሚሆን አምናለሁ::

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Share this Post