-------
በፅዳት ዘመቻ ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሂክማ ኸይረዲን፣ የአዲስ አበባ ከተማ የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ፣ የጽዳት አምባሳደሮች አርቲስቶች አትሌቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና ባለ ድርሻ አካላት ተግኝተዋል፡፡
ወ/ሮ ሂክማ በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት እንደተናገሩት ጽዳት የከተማችን መለያና የህብረተሰባችንም ባህል ሆኖ መቀጠል ይኖርበታል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
የአዲስ አበባ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ለማ በበኩላቸው ከተማችን ጽዱና ሳቢ እንድትሆን ነዋሪዎች የማይተካ ተሳትፎ እያደረጉ መሆኑን በመጥቀስ ቆሻሻን ወደ ሃብትነት ለመቀየር በተደረገው ጥረት ባለፈው የ2015 የበጀት አመት ከመልሶ መጠቀም ተግባር አንድ ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ገቢ ተገኝቷል ብለዋል።
በንቅናቄ መርሃ ግብሩ የ2015 የፅዳት ዘመቻ ውጤት በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቦም ዉይይት ተደርጎበታል፡፡
በመጨረሻም ለከተማው የጽዳት አምባሳደሮች፣ ለተፅእኖ ፈጣሪ እና ታዋቂ ግለሰቦች የአደራ ሰርቲፊኬትና የፅዳት መሣሪያዎች የማስረከብ ስነስርዓት የተካሄደ ሲሆን የበጋ ፅዳት ዘመቻው ቅዳሜ ታህሳስ 6 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም ክፍለ ከተሞች እንደሚጀመር ተገልጻል፡፡