"ለልጆች የተሻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት እንዲሁም በስፖርትና ሥነ-ምግባር የተካኑ ሀገር ተረካቢዎችን ለማፍራት ከተማ አስተዳደሩ በትኩረት እየሰራ ይገኛል።" ከንቲባ አዳነች አቤቤ

-----

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር አጎስቲኖ ፓሌሴ በየካ ክ/ከተማ ወረዳ-3 ቤላ የህፃናትና ወጣቶች የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራን መርቀው ከፍተዋል።

በአዲስ አበባ ከ1ሺ 100 በላይ መሰል የስፖርት ማዘውተሪያዎች መገንባታቸውን በመድረኩ ላይ የተናገሩት ከንቲባ አዳነች፣ ከዚህ ውስጥ ከ500 በላይ የሚሆኑት ከለውጡ ወዲህ መገንባታቸውን ገልፀው ለልጆች የተሻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት እንዲሁም በስፖርትና ሥነ-ምግባር የተካኑ ሀገር ተረካቢዎችን ለማፍራት ከተማ አስተዳደሩ በትኩረት እየሰራ ይገኛልም ብለዋል።

በከተማዋ አሁንም በቂ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እንደሌሉ የተናገሩት ከንቲባ አዳነች ይህንን በመገንባቱ ረገድ የከተማ አስተዳደሩ ከሚያከናውነው ተግባር ጎን ለጎን የተለያዩ ተባባሪ አካላት እንዲሳተፉ በቀረበው ጥሪ መሰረት የጣልያን ኤምባሲ ጥሪውን ተቀብሎ የስፖርት ማዘውተሪያውን ገንብቶ ማቅረቡን ጠቅሰው በከተማ አስተዳደሩ ስም አመስግነዋል። 

ቤላ የህፃናት እና የወጣቶች የስፖርት ማዘወተሪያ ስፍራበጣልያን አለም አቀፍ የልማት ትብብር እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፕሮጀክቶች ድጋፍ ጽህፈት ቤት ትብብር የተገነባ መሆኑም ተገልጿል።

በኢትዮጵያ የጣልያን አምባሳደር አውጎስቲኖ ፓላሴ በበኩላቸው ኤምባሲው በወንዝ ዳርቻ ልማት እና በሌሎችም መስኮች ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው ይህንን ግንኙነት አጠናክረን እንቀጥላለንም ብለዋል።

ዛሬ የተመረቀው ቤላ የህፃናት እና ወጣቶች የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ የእግር ኳስ፣ የእጅ ኳስ መጫወቻ፣ የመረብ ኳስ፣ የቅርጫት ኳስ እና የቮሊቦል ሜዳዎችን የገላ መታጠቢያዎችን እና የጂም መስሪያ ቦታውችን ያካተተ ነው።

ለበለጠ መረጃ፦

👉 YouTube https://www.youtube.com/channel/UCagI4q5d_EtvTsajRXWnFjA

👉 Tik Tok https://www.tiktok.

👉 Telegram https://t.me/AAcommu

👉 Facebook https://www.facebook.com

👉 Website https://cityaddisababa.gov.et/

Share this Post