ከአዲስ አበባ ትላልቅ ገፀ-በረከቶች (#4)

ሌላኛው የከተማችን ግዙፍ ፕሮጀክት፣ አዲስ የአፍሪካ ዓለም አቀፍ የኮንቬንሽንና ኤግዚቢሽን ማዕከል፤

=> ግንባታ ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያ በዓመት 60 ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽኖችን በተሳካ ሁኔታ እንድታዘጋጅ የሚያስችል፤

=> አዲስ አበባን የምስራቅ አፍሪቃ የግብይት እና የኢኮኖሚ ማዕከል ለማድረግ እንዲቻል ታስቦ በመሰራት ላይ ያለ፤

=> በአንድ መቶ አስር ሺህ ካሬ ሜትር መሬት ላይ እንዲያርፍ ተደርጎ በሶስት የግንባታ ምዕራፎች (3 phases) ተከፋፍሎ እየተሰራ ያለ፤

=> ሙሉ በሙሉ በከተማ አስተዳደሩ አቅም እየተሰራ ያለና ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ በጀት የተመደበለት፤

=> የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ አፈጻጸሙ 79% የደረሰና በከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ልዩ ትኩረትና ክትትል የሚደረግለት፤

=> በውስጡ የዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽንና ባዛር መዳረሻዎች እና ግዙፍ የገበያ ሞሎች እንዲሁም 10 ሺህ የሚልቁ እንግዶችን በአንድ ቦታ ለማስተናገድ የሚያስችል አቅም ያለው፤

-------

በአዲስ አበባ ከተማ እየተገነቡ ካሉ ግዙፍ የሜጋ ፕሮጀክቶች መካከል የአዲስ አፍሪካ ዓለም አቀፍ የኮንቬንሽንና ኤግዚቢሽን ማዕከል አንዱ ነው።

የዲስ አፍሪካ ዓለም አቀፍ የኮንቬንሽንና ኤግዚቢሽን ማዕከል ግንባታው ተጠናቆ በሙሉ አቅሙ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር ሀገራችን ኢትዮጵያ እንዲሁም ከተማችን አዲስ አበባ ልዩ ልዩ ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽኖችና ባዛሮችን በተሳካ ሁኔታ ማስተናገድ እንድትችል የላቀ አስተዋጽኦ የሚያበረክት ይሆናል፤

ልዩ ልዩ ዓለም አቀፍ ሁነቶችን ለማሰናዳት ከተማችንን አቋርጠው የሚያልፉ የነበሩ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ደንበኞችን እዚሁ በመዲናችን በማስቀረት ሀገራችን የውጭ ምንዛሪ በሚፈለገው ደረጃ ማግኘት እንድትችል ልዩ አቅም የሚፈጥር ይሆናልም ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል።

የአዲስ አፍሪካ ዓለም አቀፍ የኮንቬንሽንና ኤግዚቢሽን ማዕከል ግንባታ ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያ በዓመት 60 ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽኖችን በተሳካ ሁኔታ ለማዘጋጀት ያስችላል፤

ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን የሚያሟላ መሰረተ ልማት ማዕከሉ የሚዘረጋለት ሲሆን በሁሉም ረገድ ከምስራቅ አፍሪቃ ተወዳዳሪ ማዕከል ይህናል።

የአዲስ አፍሪካ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽንና ኤግዚቢሽን ማዕከል የመጀመሪያ ዙር ግንባታ 2016 . የሚጠናቀቅ ሲሆን አጠቃላይ ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር ኢትዮጵያ በዓመት 60 ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽኖችን ማዘጋጀት እንድትችል አቅም ይሆናል።

የአዲስ አፍሪካ ዓለም አቀፍ የኮንቬሽን ሴንተር ፕሮጀክት በአንድ መቶ አስር ካሬ ሜትር መሬት ላይ እንዲያርፍ ተደርጎ በሶስት የግንባታ ምዕራፎች (3 phase) ተከፋፍሎ ርብርብ እየተደረገለት የሚገኝ ከመሆኑም በላይ ሲጠናቀቅ የከተማችን ልዩ ድምቀትና ውበት እንዲሁም የሀገራችንን ገጽታ ለማሻሻል አቅም ይሆናል ተብሎ የታመነበት ፕሮጀክት ነው።

የፕሮጀክቱ ምዕራፍ አንድ (phase 1) ግንባታ ስራ በሚፈለገው ፍጥነትና ጥራት በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል።

የአዲስ አፍሪካ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽንና ኤግዚቢሽን ማዕከል የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ በመጪው ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ተጠናቆ ወደሚቀጥለው የግንባታ ምዕራፍ ሽግግር ያደርጋል፣

በማዕከሉ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ 12 ሺህ በላይ ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፉ ልዩ ልዩ ኤግዚቢሽንና ዓለም አቀፍ ባዛር ማሳያዎችን ጨምሮ የሁለገብ አዳራሾች ግንባታ እየተገነባ ሲሆን የግንባታው የመጀመሪያ ምዕራፍ ሲጠናቀቅ ከአንድ ሺህ በላይ ታዳሚዎችን መያዝ የሚችል እና 7 ሺህ ካሬ ሜትር ስፋት ያለው አንፊ ቲያትርን የሚያካትትም ይሆናል።

አዲስ አበባን የምስራቅ አፍሪቃ የግብይት እና የኢኮኖሚ ማዕከል ለማድረግ እንዲቻል ታስቦ እየተሰራ የሚገኘው ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት በከተማ አስተዳደሩ ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ በጀት የተመደበለት ነው።

ማዕከሉ በውስጡ የዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽንና ባዛር መዳረሻዎች እና ግዙፍ የገበያ ሞሎች እንዲሁም 10 ሺህ የሚልቁ እንግዶችን በአንድ ቦታ ለማስተናገድ የሚያስችል አቅም ይኖረዋል፤

የማዕከሉ ግንባታ ሁለተኛ ምዕራፍ በቅርብ ሲሚጀመር በተመሳሳይ ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን የሚያሟላ የኮንፍረንስ ማዕከል ይኖረዋል፤

የአዲስ አፍሪካ ዓለም አቀፍ የኮንቬሽንና ኤግዚቢሽን ማዕከል ከኤግዝብሽንና ባዛር አገልግሎት በተጨማሪ ለመዝናኛ እና ቲያትር፣ ለፊልም ማሳያና ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ሰፋፊ አዳራሾች ይኖሩታል፤

ከሶስት ሺህ 500 በላይ ተታዳሚዎችን በተመሳሳይ ግዜ ማስተናገድ የሚችሉ አዳራሾችን ጨምሮ እስከ 100 ሰው ማስተናገድ የሚችሉ ስድስት የስብሰባ አዳራሾችም የግንባታው ሁለተኛ ምዕራፍ አካል ናቸው።

የአዲስ አፍሪካ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽንና ኤግዚቢሽን ማዕከል ሁለተኛ ምዕራፍ ግንባታ ሲጠናቀቅ በአጠቃላይ ማዕከሉ 27 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፍ ይሆናል

ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሽርክና ከሚያስገነባቸው የመዲናዋ ትላልቅ ፕሮጀክቶች መካከል ፣ግንባር ቀደምም ሲሆን፤ አጠቃላይ ግንባታው ሲጠናቀቅ የከተማዋ ሁለንተናዊ ገፅታ ላይ ተደማሪ አቅም የሚፈጥር ከመሆኑም ባሻገር በልዩ ልዩ የሙያ መስክ ለተሰማሩ የከተማችን ነዋሪዎችና ብሎም አገገራችን ዜጎች ቋሚ እና ጊዚያዊ የስራ እድል ይፈጠራል።

Share this Post