27
Nov
2022
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በምልከታቸው በክፍለ ከተማው በዘጠና ቀናት እቅድ ተካተው ወደ ተግባር ተገብቶ እየተከናወኑ የሚገኙ የአገልግሎት ማሻሻያ ፣ የመልካም አስተዳደር ፣ የከተማ ግብርና፣የዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎችን ታሣቢ ያደረጉ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እንዲሁም ሌሎች ሰው ተኮር ተግባራት በክፍለ ከተማው እየተሠሩ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸውም በዘጠና ቀናት እየተሠሩ ያሉ ስራዎች በእቅዳቸው መሠረት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ለመገንዘብ ተችሏል።