19
Dec
2022
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየደረጀው ከሚገኙ የትምህርት ማህበረሰብ አካላት ጋር የጀመረውን ውይይት አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በሌላ በኩል በዛሬው እለት በሁሉም ክ/ከተሞች በትምህርት ቤቶች የተረጋጋ እና ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ እያካሄደው ባለው በዚሁ ውይይት ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ እንደገለፁት የከተማ አስተዳደሩ ከነሃሴ 2014 ጀምሮ በኮተቤ ዩንቨርሲቲ ሲያስጠናው የቆየውን የብዝሀ ቋንቋ ካሪኩለም አጠናቆ በዚህ ሳምንት ለውይይት እንደሚያቀርብ አስታውቀዋል፡፡
ይህ ካሪኩለም ፀድቆ ወደ ትግበራ የሚገባና በተለይም የከተማዋን ብዝሃነት በብቃት የሚያስተናግድ ስርዓት የሚተገበር መሆኑን የገለፁት ዶ/ር ዘላለም በተለይም በትምህርት ሚኒስቴር የቋንቋ ፖሊሲ መሰረት 3 ቋንቋዎችን ራሳቸውን ችለው እንደ አንድ የትምህርት አይነት በትምህርት ቤቶች እንዲሰጡ ለማድረግ እና የባንዲራ እና የመዝሙሩም ጉዳይም መፍትሄ የሚሰጥ መሆኑንም ሃላፊው ጠቁመዋል፡፡