በአዲስ አበባ የመግቢያ በሮች ላይ አራት ሜጋ ሁለገብ የግብርና ምርቶች ማከፋፈያ የገበያ ማዕከላትን እየገነባን ነው፡፡

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሁለት፣ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አንድ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አንድ በግንባታ ላይ ይገኛሉ፡፡

እነኚህ የገበያ ማእከላት ከፍተኛ የግብርና ምርትን በመያዝ፣ የኑሮ ውድነቱን ጫና በመቀነስ፣ ገበያን በማረጋጋትና በመቆጣጠር የራሳቸውን ሚና የሚጫወቱ ብሎም ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የስራ እድልን የሚፈጥሩ ይሆናሉ፡፡

ግንባታቸውም በታለመለት ጊዜና ወጪ እንዲጠናቀቅ የጀመርነውን የቅርብ ክትትልና ድጋፍ አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Share this Post