በአዲስ አበባ የብዝሀ ቋንቋ ስርዓተ ትምህርት ለመተግበር እየተደረገ ላለው የዳሰሳ ጥናት የግብዓት ማሰባሰቢያ የምሁራን መድረክ እየተካሄደ ነው

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቤቶች የብዝሀ ቋንቋ ስርዓተ ትምህርት ለመተግበር የተካሄደ የዳሰሳ ጥናት ውጤት ግብዓት ማሰባሰቢያ የምሁራን መድረክ እየተካሄደ ነው።

የብዝሀ ቋንቋ ስርዓተ ትምህርት ለመተግበር የተካሄደውን የዳሰሳ ጥናት በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ አማካኝነት ከሀምሌ 2014 . ጀምሮ ሲያካሂድ መቆየቱ ተነግሯል።

ጥናቱ በስርዓተ ትምህርት ውስጥ አንድ የሀገር ውስጥና አንድ የውጪ ቋንቋ ለማካተት የተደረገ ጥናት መሆኑን የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት / ብርሀነ መስቀል ጠና ተናግረዋል።

2014 ግንቦት ወር ላይ የተጀመረው ጥናቱ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ሀሳቦች በግብአትነት የወሰደ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለትም ከምሁራን ሀሳቦችን ለማሰባሰብ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።

ቋንቋ ለማህበራዊ ብቻም ሳይሆን ለኢኮኖሚውም ወሳኝ በመሆኑ፤ በስርዓተ ትምህርት ውስጥ የሚካተቱት ቋንቋዎች በሚገባ ታስቦባቸው የሚተገበሩ ናቸው ሲሉም / ብርሀነ መስቀል ጠና ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ / ዘላለም ሙላቱ፥ የኮተቤ ዩኒቨርሲቲ አሳታፊ በሆነ መልኩ የብዝሀ ቋንቋ ስርዓተ ትምህርት ጥናት ሲያካሂድ ቆይቷል ብለዋል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ / ሳሙኤል ክፍሌ በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የተገኘው ግብዓት ለሌሎች አካባቢዎችም ምሳሌ ይሆናል ብለዋል።

ህጻናትን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ማስተማር የፖሊሲው እቅድ ነው፤ ነገር ግን አተገባበሩ ውይይት ያስፈልገዋል ሲሉም ተናግረዋል።

ምሁራኑም በእውቀት ላይ የተመሰረተ እና ከስሜት የፀዳ አስተያየት በመስጠት ለግብዓት ማሰባሰቡ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም አሳስበዋል።

Share this Post