28
Dec
2022
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተገንብቶ በክቡር ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ለምረቃ የበቃው ዘመናዊው የአንድነት መኪና ማቆሚያ፣ አሁን ላይ ደንበኞች አስፈላጊውን ክፍያ በመፈጸም አገልግሎቱን እንዲያገኙ እየተደረገ ነው ፡፡
በአካባቢው ያሉ የሳይንስ ሙዚየም ፣ አንድነት ፓርክ ፣ወዳጅነት ፓርክ ፣ የንግድ ተቋማት፣ ቤተ እምነቶችና ሌሎች ተቋማት የሚገኙ እንደመሆኑ የአንድነት መኪና ማቆሚያ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ጠቀሜታውን የጎላ ያደርገዋል፡፡
ይህ ከታላቁ ቤተ መንግስት አጠገብ የሚገኘው የመኪና ማቆሚና ሁለገብ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል አቅም ያለው ህንፃ ሲሆን፤ በዋናነት በአካባቢው ያለውን የትራፊክ ፍሰት ከማሳለጥ ባሻገር ለደንበኞች ንብረት ደህንነት መጠበቅ፤ ለዜጎች ስራ እድል መፍጠርና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች ያሉት ግዙፍ የመዲናችን ፕሮጀክት ነው፡፡
የመኪና ማቆሚው በመጀመሪያው ወለል ላይና ከታች ባሉ አራት ተከታታይ የምድር ወለሎች አውቶቡሶችን ጨምሮ በአጠቃላይ ከ1ሺህ 20 በላይ ተሽከርካሪዎችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ የሚችል ነው፡፡