01
Jan
2023
በዚህም የኮልፌ መንዲዳ ሆስፒታልን ፣የላፍቶ ሆስፒታል ግንባታን ፣የኮልፌ እና ላፍቶ የገበያ ማዕከል ግንባታን ፣ ለአርሶአደር የልማት ተነሺዎች ማቋቋምያ ማዕከልን ፣ እንዲሁም በከተማችን የመጀመሪያ የሆነውንና ለስራ እድል ፈጠራ ትልቅ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ተስፍ የተጣለበት የኢንደስትሪ ክላስተርን ፕሮጀክቶች ተመልክተናል ፡፡
ፕሮጄክቶቹ በአጠቃላይ ከ10 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎባቸው እየተገነቡ የሚገኙ ሲሆን አብዛኛው አፈፃፀማቸው ጥሩና ተስፍ ሰጪ ሲሆኑ በልዩ ትኩረት እየተሰሩ እንዳሉ ገምግመናል።
በሆስፒታሎች ግንባታ ላይ የሚታየዉን መጓተት በፍጥነት መስተካከል እንዳለበት ከኮትራክተሮች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርገን ችግሩን ለመፍታት ተስማምተናል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!!
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ