የገና ስጦታ

ከንቲባ / አዳነች አቤቤ የገና በዓን አስመልክተው ለአምስት ታላላቅ የኪነጥበብ ባለሙያዎችና ቤተሰቦች የመኖርያ ቤት ስጦታ አበረከቱ፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሃገራቸውን በከፍተኛ ደረጃ ሲያገለግሉ የቆዩና በአሁን ሰዓት አስታዋሽ አጥተው በተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ወድቀው ላሉ የሃገር ባለውለታ አምስት ታላላቅ የኪነጥበብ ሰዎች ለሃገራቸው ስዋሉት ከፍ ያለ ውለታ የመኖርያ ቤት ስጦታ የገና በዓልን አስመልክቶ ተበርክቶላቸዋል፡፡

እነዚህም አርቲስቶች

1 አርቲስት ይልማ ግብረዓብ

2 አርቲስት ጌታቸው ካሳ

3 አርቲስት አሸናፊ ከበደ

4 አርቲስት መስፍን ጌታቸው (በቅርቡ ከዚህ አለም ቦት የተለየ) ለወላጅ እናቱ ለወ/ ሎሚ /መስቀል ብራ

5 አርቲስት ሻምበል በላይነህ

ከንቲባ / አዳነች አቤቤ ለነዚህ የሃገር ባለውለታ አርቲስቶች የመኖርያ ቤት ከነሙሉ እቃው ካዛንቺስ አካባቢ ራሳቸው ከንቲባ አዳነች አቤቤ በጎ ፈቃደኞችን አስተባብረው ባስገነቡት ህንፃ ላይ በዛሬ እለት አስረክበዋል፡፡

መልካም አመት በዓል፡፡

Share this Post