08
Jan
2023
በዛሬው እለት የመሰረተ ድንጋይ የተጣለው የሴቶች የተሃድሶና የስልጠና ማዕከል በሚገነባበት ቦታ ላይ የነበረው የአረጋውያን ማእከል በአዲስ እና እጅግ ዘመናዊ ማእከል እንደሚተካ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል፡፡
ነባሩ የአረጋውያን ማእከል ውስጥ 150 አረጋውያን ብቻ የነበሩ ሲሆን በአዲስ መልኩ በተገነባው በሰንሻይን ኮንስትራክሽን ትብብር በተገነባውና ከ750 በላይ አረጋውያን የመያዝ አቅም ያለው ባለውና አረጋውያን በስራ ፈጠራ እንዲሳተፉ ተቋሙ ራሱን የሚያስተዳድርበት ሁኔታ የተመቻቸለት ተቋም ሲሆን የራሱ የንግድ ሞል የሚኖረውም ስለመሆኑ ተጠቅሷል፡፡
በዚሁ ስስርዓት ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማዕከሉ የሚኖሩ የጎዳና ተዳዳሪዎችን የእንኳን አደረሳችሁና የምሳ ግብዣ አከናውነውላቸዋል፡፡
ዛሬ በተጀመረውና በሚገነባው የሴቶች ማገገያ ማዕከልም ላይ በስራ ዕድል ፈጠራ ተሳትፎ እንዲያደርጉ እድል መመቻቸቱን አስታውቀዋል፡፡