በዴንቨር ከተማ ከንቲባ ሚስተር ሚካኤል ቢ ሐንኮክ ለተመራ የልኡካን ቡድን በከንቲባ ፅ/ቤት የአስተዳደሩ የካቢኔ አባላት በተገኙበት አቀባበል አድርገንላቸዋል፡፡

አርማችን የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዴንቨር አዲስአበባ በጀመረው አዲስ የበረራ መስመር የሁለቱን ከተሞች የሁለትዮሽ ግንኙነትን ለማጠናከር ወደ ከተማችን የመጣው በከንቲባ ሚስተር ሚካኤል ሐንኮክ የተመራ የልኡካን ቡድን፣ በዛሬው እለት በፅ/ቤታችን በነበራቸው ቆይታ፤ ከከተማችን አስተዳደር ካቢኔ ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን የሚያጠናክር ፍሬያማ ውይይት አካሂደናል፡፡

ክቡራን እንግዶቻችን እንኳን ወደ ከተማችን አዲስ አበባ በደህና መጣችሁ፤ ቆይታችሁ አስደሳች እንዲሆን እመኛለሁ!!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!!

Today, we welcomed a delegation led by the Mayor of Denver, Mr. Michael B. Hancock, to the Mayor's Office in the presence of the administration's cabinet members.

The main purpose of the visit is to strengthen the bilateral relations between the two cities and the new flight route that Ethiopian Airlines has launched from Denver to Addis Ababa.

The delegation led by Mayor Mr. Michael B. Hancock, which included various officials, visited our office today had a fruitful discussion that will strengthen our bilateral relations.

Dear guests, welcome to our city, Addis Ababa, I wish you a bright and pleasant stay.

May the God bless Ethiopia and its people!

ከንቲባ / አዳነች አቤቤ

Share this Post