ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዛሬው እለት የሞዛምቢክ ኬሊማን ከተማ ከንቲባ የሆኑትን ሚ/ር ማኑኤል ዲ አራዦን በፅ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

የኬሊማን ከተማ ከንቲባ / ማኑኤል አራዦን በዚሁ ወቅት አዲስ አበባ ከተማ እያስመዘገበች ስላለችው ሁለንተናዊና አስደናቂ የለውጥ እንቅስቃሴ የተሰማቸውን አድናቆት ገልፀዋል፡፡ ይህንም ተሞክሮም ሊሰፋ እንደሚገባው ተናግረዋል፡፡

በውይይታቸው በሁለቱ ከተሞች መሀከል በኢንቨስትመንት ፤በኮንስትራክሽንና ሪልስቴት በባህል ልውውጥ እንዲሁም የእህትማማችነትን ግንኙነትን በማጠናከርና በሌሎችም የሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙርያ መክረዋል፡፡

Share this Post