የህብረት ስራ ማህበራትን ማጠናከር ህብረተሰብን መደገፍ ነው፡፡

2ኛውን ከተማ አቀፍ የህብረት ስራ ማህበራት ኤግዚቢሽንና ሲምፖዚየም በኤግዚቢሽን ማዕከል በይፋ አስጀምረናል።

በከተማችን አዲስአበባ ፍትሃዊ የግብይት ስርዓት እንዲኖር በማድረግ ሰው ሰራሽ የኑሮ ውድነት ጫናን በማቃለል፣ ለህብረተሰቡ ምርትንና ሸቀጥን በየአካባቢው በእሁድ ገበያ እና በሸማች ሱቆች አማካኝነት ተደራሽ በማድረግ ረገድ የህብረት ስራ ማህበራት የማይተካ ሚና አላቸው ፡፡

በዚህ አጋጣሚ ሁላችንም አብሮነታችንን በማጠናከር ለህዝባችን ኑሮውን የሚያቃልል ስራ እንጂ የሚያከብድ ተግባር ላይ እንዳንሰማራ አደራ ለማለት እወዳለሁ!!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

 

 

Share this Post