20
Feb
2023
በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ሽልማት ሰጥተናል።
በ2014 የትምህርት ዘመን ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ 896,520 የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል በሃገር አቀፍ ደረጃ ከ600 በላይ ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር 273 ሲሆን ከእነዚህ ተማሪዎች መካከል 125 ተማሪዎች ከአዲስ አበባ ከተማ ናቸው። በሃገር አቀፍ ደረጃ ፈተና ከወሰዱት ውስጥ ያለፉት 3.3% ሲሆኑ እንደ አዲስ አበባ 19.8 % ናቸው።
ያሰብነው ውጤት ባይመጣም ዛሬ የሸለምናቸው በፈተና ውስጥ ያለፋ እንቁዎች ስለሆኑ ነው።
ገና ብዙ መስራት የሚጠበቅብን በመሆኑ በቀጣይ ከዚህ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ የትምህርት ባለድርሻ አካላት፣ መምህራን፣ ወላጆች እንዲሁም ተማሪዎች የበኩላችሁን አስተዋጽዖ ልትወጡ ይገባል ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!!
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ