02
Apr
2023
ከንቲባ አዳነች በክፍለ ከተማው የሚገኙ ባለሃብቶችን በማስተባበር በስድስት ብሎኮች የተገነቡ ቤቶች ለአቅመ ደካሞች፥ ለውስብስብ የጤና እክል የተዳረጉ የህብረተሰብ ክፍሎች፥ እና በከተማው እየተከናወነ በሚገኘው የወንዝ ዳርቻ ልማት ለተነሱ ነዋሪዎች ተላልፈዋል።
ዛሬ የቤት ባለቤት ከሆኑት ውስጥ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በነበረው ጦርነት ወላጆቻቸውን ያጡ ህጻናት ይገኙበታል።
በተጨማሪም በክፍለ ከተማው ተለይተው በዛሬው ዕለት የቤት ቁልፍ ለተቀበሉ ነዋሪዎች ከንቲባ አዳነች የማዕድ ማጋራትንም አድርገዋል ።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ በተጠየቁ ጊዜ በበጎነት አቅማቸውንና ገንዘባቸውን ላበረከቱ የክፍለ ከተማው ባለሃብቶች ምስጋና አቅርበዋል።
የከተማ አስተዳደራችን ቀዳሚ ትኩረት ያለንን ሀብት በፍትዊነት ለነዋሪዎች ተደራሽ ማድረግ ነው ብለዋል ከንቲባ አዳነች።
የከተማችንን የቱሪዝም ልማትና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት በጽኑ የምንፈልግ ሁላችን የልማት ተባባሪ መሆን ይጠበቅብናል ሲሉም ተናግረዋል።
ኃይላችንን አሰባስበን ከተባበርን ከተማችንን በሚፈለገው ደረጃ መለወጥ እንችላለን ያሉት ከንቲባዋ በሂደት በሁሉም ደረጃ የሚገኙ የከተማችንን ነዋሪዎች የቤት ፍላጎት ለማሟላት አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅቶችን አጠናቀን ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ገብተናል ሲሉ ገልጸዋል ።