ዛሬ ከፍል ውሃ አካባቢ፣ ከጉለሌ እና ከአራዳ ክፍለከተሞች

በልማት እና ከወንዝ ዳርቻ ለተነሱ የከተማችን ነዋሪዎች 200 ምትክ መኖሪያ ቤት፣ 525 ኮንዶሚኒየም ቤት፣ ለግል ይዞታ ባለቤቶች 1.1 ቢልዮን ብር ካሳና. 5.6 ሄክታር ምትክ መሬት አስረክበናል።

የወንዞቻችን ዳርቻ አካባቢዎች በደረቅና ፍሳሽ እንዲሁም ከፋብሪካ በሚለቀቁ ቆሻሻዎች በመበከላቸው በሰው ልጅ ላይ የጤና ችግር የሚያስከትሉ፣ በዝናብ ወቅት በሰውና በንብረት ላይ አደጋ የሚያደርሱ ሲሆን ይህን በመቅረፍ የነዋሪዎቻችንን ህይወት ከአደጋ ለመታደግ በገባነው ቃል መሰረት እና ከተማዋን ንጹህ ውብና አረን እንዲሁም ለኑሮ ምቹ እና የቱሪስትት መስህብ ለማድረግ ከእንጦጦ እስከ ወዳጅነት ፓርክ 5.5 . ርዝመት ያለው የወንዝ ዳርቻ ልማት ስራ ጀምረናል።

በዚህ ልማት ሳቢያ ለተነሱ ነዋሪዎች የግል ይዞታ ለነበራቸው 1.1 ቢልዮን ብር የንብረት ካሳ ከፍለን 5.6 ሄክታር ምትክ መሬት በመረጡት አካባቢ ሰጥተናል።

200 ለሚሆኑ ነዋሪዎች ለመኖር ምቹ የሆነ ዘመናዊ የመኖሪያ ቤቶች አስረክበናል።

ኮንዶሚኒየም ቤት ለመረጡ 525 ነዋሪዎች ጥያቄያቸውን አሟልተን የቤታቸው ግንባታ እስኪጠናቀቅ 5 ወራት የሚሆን የቤት ኪራይ 36.6 ሚሊዮን ብር ከፍለናል።

በተግባር የነዋሪዎቻችንን ችግር ደረጃ በደረጃ በመቅረፍ ሁሉም በፍትሃዊነት ተጠቃሚ የሚሆንባት ከተማ መገንባታችንን እንቀጥላለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ / አዳነች አቤቤ

Share this Post