09
Apr
2023
በህዝብ ጥያቄ የጀመርናቸው ዘመናዊ ሆስፒታሎችን፣ የከተማችንን የግብርና ምርት አቅርቦት ችግር ለመፍታት ወሳኝ ሚና ያላቸው የገበያ ማዕከላትን ፣ ለስራ እድል ፈጠራ እና ለምርት አቅርቦት ትልቅ ሚና ያለው የኢንዱስትሪ ክላስተርን፣ የመንገድ ፕሮጀክቶችን፣ የአመራሮቻችንን ብቃት ለመገንባት የሚያግዝ አካዳሚን ጨምሮ የሌሎች ፕሮጀክቶች አፈጻጸም በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ግንባታቸው እየተከናወነ መሆኑን ተመክተናል።
መጀመር ብቻ ሳይሆን በጊዜ የማጠናቅቅ ልማዳችንን በማጠናከር ፕሮጀክቶቻችን በተያዘላቸው ጊዜ እና በተመደበላቸው በጀት በጥራት ግንባታቸው እየተፋጠነ ይገኛል። እነዚህ ፕሮጀክቶች የከተማችንን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የሚያቀለጣጥፉ፣ የህዝቡን የኑሮ ሸክም የሚያቀሉ፣ የስራ ዕድል የሚፈጥሩ እንዲሁም የከተማችንን ገጽታ የሚያሻሽሉ ናቸው።
የከተማችንን ነዋሪዎች በታማኝነት እና በትጋት ለማገልገል የገባነውን ቃል በተግባር እንድንፈጽም የደገፋችሁን ሁሉ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ።
ከንቲባ ኣዳነች አቤቤ