20
Jun
2023
በመጀመሪያ ምዕራፍ የአረንጏዴ አሻራ ከ41 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል ግባችንን አሳክተናል።
የሁለተኛው ምዕራፍ ደግሞ መላው የከተማችን ነዋሪዎች በሚሳተፉበት 17 ሚሊዮን ሀገር በቀል ዛፎችን፣ ለምግብነት የሚውሉ እና ለውበት የሚሆኑ ችግኞችን አዘጋጅተናል። አዲስ አበባን አረንጓዴ በማልበስ ለነዋሪዎቿ ምቹ እና ውብ ከተማ ለማድረግ፣ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም፣ የሥራ ዕድል ለመፍጠር እንዲሁም የምግብ ዋስትናችንን ለማረጋገጥ ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን ተንከባክበን እንዲጸድቁ እና ፍሬ እንዲያፈሩ ማድረግ የሁላችንም ሃላፊነት ነው። በመሆኑም የከተማችን ነዋሪዎች በትጋት ችግኝ እንድትተክሉ እና እንድትንከባከቡ ጥሪ አደርግላቹሃለሁ።
የሰነቅነውን ራዕይ እውን ለማድረግ ፈተናዎቻችንን በድል እየተሻገርን፣ ነጋችንን ዛሬ እየሰራን መጓዛችንን እንቀጥላለን!
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ