ከንቲባ አዳነች አቤቤ "ዛሬ በአብርሆት ቤተ መጻህፍት የዲጂታላይዚሽን አገልግሎት ስራ አስጀምረናል ::

ቤተ መጻህፍቱ አሁን በሚሰጠው አገልግሎት በአማካይ በቀን 15 ሺህ በላይ አንባቢዎችን የሚያስተናግድ ሲሆን ዛሬ ባስጀመርነው 80 ሺህ መፅሃፍት ዲጂታል የተደረገበት አገልግሎት ከእጥፍ በላይ አንባቢዎችን መድረስ ያስችለናል::

ትውልዱ የሚያነብበት ስፍራ በማጣቱ እንጂ ሁኔታዎች ከተመቻቹለት በንባብ ራሱን ለማነጽ የሚተጋ መሆኑን በማየታችን ፤ተጨማሪ አዳዲስ ቤተመጻህፍት በየክፍለከተሞቻችን እየገነባን የተጠናቀቁትንም በቁሳቁስ እንዲሟሉ በማድረግ አንባቢ እና ምክንያታዊ ትውልድ ማፍራታችንን እንቀጥላለን::"

 

Share this Post