05
Jul
2023
- ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በስማርት ሲቲ እና ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፅንሰ ሃሳብ ላይ ያተኮረ የግንዘቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለባለድርሻ አካላት ተሰጥቷል::
በግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ምቹ እና አገልግሎት አሰጣጡን ዘመናዊ ፣ ፈጣን እንዲሁም ዜጎች ያለምንም እንግልት አገልግሎት እንዲያገኙ የቴክኖሎጂ ስራዎች በተደራጀ ሁኔታ የነዋሪዉን ፍላጎት በሚያሟላ መልክ እንዲተዳደር በጥናት ተደግፎ አዲስ አደረጃጀት በመፍጠር ሥራዎችን እየሰራን እንገኛለን
የከተማ አስተዳደሩ አገልግሎት አሰጣጡን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ይበልጥ ለማዘመን ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች ተቋማት አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ስራ ላይ በማዋል የህዝቡን እንግልት የሚቀንሱ አሰራሮችን ዘርግተዋል ብለዋል::