በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለከተማ ቤተል አካባቢ እና በለሚ ኩራ ክፍለከተማ አያት አካባቢ ግንባታቸው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙ ግዙፍ የግብርና ምርት የገበያ ማዕከላት ያሉበትን ሁኔታ ተዘዋውረን ጎብኝተናል።

እነዚህ በመገንባት ላይ የሚገኙት የግብርና ምርት የገበያ ማዕከላት፣ ምርትን በስፋት ወደ ከተማችን ማስገባት ከማስቻል እና በከተማችን ያለውን ህገወጥ የገበያ ትስስር ሰንሰለት ከማስቀረት በተጨማሪ የኑሮ ጫናን የሚያቃልሉና ለነዋሪዎቻችን ተጨማሪ የስራ እድል የሚፈጥሩ ናቸው።

ለህዝባችን በገባነው ቃል መሰረት የጀመርናቸው ፕሮጀክቶቻችንን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ተግባራዊ በማድረግ በተያዘላቸው ጊዜ በጥራት በማጠናቀቅ በቅርብ ቀን ለአገልግሎት ክፍት እናደርጋለን።

በመጨረሻም የኦቪድ ኮንስትራክሽን ግሩፕ ላሳየዉ የግንባታ ብቃት እናመሰግናለን።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

 

Share this Post