15
Aug
2023
የአድዋ ድልን ታሪካዊ ዳራ መነሻ አድርጐ እየተገነባ የሚገኘው አድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚየም የኢትዮጵያ ጀግኖችንና የአድዋ መልክዓ ምድርን በሚገልፅ መልኩ ታሪካዊ እሴቱን ጠብቆ ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል።
ሙዚየሙ በከተማችን ውስጥ እስከዛሬ ከተገነቡ እና በመገንባት ላይ ከሚገኙ ፕሮጀክቶች ግዙፉ ሲሆን 11 ብሎኮችን የያዘ 45000 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ እየተገነባ ያለ በውስጡ የአድዋ ሰንሰለታማ ተራሮችን፣ የአድዋ ፈረሰኞች ማስታወሻ፣ ለሴት ጀግኖች ክብር የተሰየመ ማስታወሻ፣ የአንድነት ማዕከል፣ የአፍሪካ ነፃነት ማስታወሻ እንዲሁም የኢትዮጵያ ጀግኖችን ጉዞ የሚያሳይ ሙዚየም እንዲሁም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ከ300 እስከ 4000 ሰው ድረስ የሚይዙ የተለያዩ አዳራሾች የሚገኙበት ሲሆን ግንባታው በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት የሚደረግ ይሆናል::
መጪውን የአድዋ በዓል የጥቁር ህዝቦች የድል የታሪክ ከፍታን በሚመጥን መልኩ በዚሁ ስፍራ ላይ በጋራ እናከብራለን።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ