16
Aug
2023
ሌጀንድ ማርሻል አርት አካዳሚ ኤንድ ፌዴሬሽን ፣ ኮምፖዚት ማርሻል አርት ፌዴሬሽን፣ ኢንተርናሽናል ፕሮ ቴክዋንዶ ፌዴሬሽንና ሁንጊ ቴክዋንዶ ፌዴሬሽን ከንቲባ አዳነች በከተማዋ ስፖርት ማስፋፋት የሚያስችሉ የማዘውተሪያና የወጣቶች ስብዕና ግንባታ ማዕከላትን በማስገንባታቸውና በስፖርት ዘርፍ መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት የሚያስችሉ ስራዎችን በመስራታቸው ሽልማቱ መሰጠቱን ግራንድ ማስተር ሔኖክ ኃይለየሱስ የሌጀንድ ማርሻል አርት አካዳሚ ፕሬዚዳንት ገልጸዋል፡፡
የስፖርት ፌዴሬሽኖቹ ከስፖርታዊ ውድድርና ልማት ባሻገር በሚሰሯቸው የበጎ ፈቃደኝነት ስራዎች ላይ ከንቲባ አዳነች እየሰሩት ያለውን ስራ እንደሚደግፉ ግራንድ ማስተር በፍቃዱ ታደሰ የሌጀንድ ማርሻል አርት ምክትል ፕሬዚዳንት ገልጸዋል፡፡
ፌዴሬሽኖቹ ለከንቲባ አዳነች አቤቤ 7ኛ የክብር ዳን ፣ የምስጋና ሰርትፌኬትና የሜዳልያ ሽልማት አበርክተዋል፡፡