"አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ተምሳሌት"

"አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ተምሳሌት" በሚል መሪ ቃል የኢ.ፕ.ድ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የፓናል ውይይት እና የፎቶግራፍ አውደ-ርዕይ መርሐግብሮች በዛሬ እለት ይካሄዳሉ።

የፓናል ውይይቱ በሳይንስ ሙዚየም የሚካሄድ ሲሆን፣ የፎቶ አውደ ርዕዩ ደግሞ በመስቀል አደባባይ የሚከፈት ይሆናል።

በፓናል ውይይት መድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የክልል ፕረዘዳንቶች፣ የፌዴራል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች የሚሳተፉ ሲሆን በመስቀል አደባባይ የሚከፈተው የፎቶ አውደ-ርዕይ እስከ ጳጉሜን 6 ለጎብኚዎች ክፍት ይሆናል።

Share this Post