የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ መከበሩን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልፀዋል፤

ከንቲባ አዳነች ለሚዲያ አካላት በሰጡት መግለጫ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች የታደሙበት የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል እሴቱን ጠብቆ እንዲከበርና በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋፅኦ ያበረከቱ አካላትንም አመስግነዋል።

ከንቲባ አዳነች አክለውም በከተማችን የተከበረውና ሚሊዮኖች የተሳተፉት የኢሬቻ በዓል እጅግ ደማቅ፣ ፍፁም ሰላማዊ፣ እሴቱን የጠበቀ እና ወንድማማችነት እና እህትማማችነት ጎልቶ የታየበት ሆኖ ተከብሯልም ብለዋል።

ለበዓሉ ድምቀት መላው የኦሮሞ ህዝብ፣ አባ ገዳዎች፣ ሃደ ሲንቄዎች፣ ፎሌዎች፣ መላው የከተማችን ነዋሪ ላሳየው የእንግዳ አቀባበል፣ የፀጥታ አካላት እና ሚዲያዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻዎች ላደረጉት አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

አዲስ አበባ ከተማችን በሳምንት ልዩነት ውስጥ እንደ መስቀል ደመራ እና ኢሬቻ የመሳሰሉ ታላላቅ ህዝባዊና ሐይማኖታዊ የአደባባይ በዓላት እሴቶቻቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ ያስቻለች ሲሆን ከነዚህ ታላላቅ በዓላት ከተማዋ የምታገኘው የቱሪዝም ገቢም እያደገ መምጣቱን ገልፀዋል።

Share this Post