16
Oct
2023
የአዲስ አበባ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ በዜና አልቃድር ይህንን ያሉት በአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት- ሰራተኞች ፣የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣በሁሉም ማዕቀፍ የሚገኙ የፖሊስ አባላትና ሌሎችም የሚመለከታቸው ሁሉ በተገኙበት 16ኘው ሀገር አቀፍ የሰንደቅ -ዓላማ ቀን በተከበረበት ወቅት ነው።
በሀገር አቀፍ ደረጃ የኢፌዴሪ የሰንደቅ-ዓላማ ቀለን ለ16 ግዜ መከበሩ የሚታወስ ሲሆን ዘንድሮም "የሰንደቅ -ዓላማችን ከፍታ ለሕብረብሔራዊ አንድነታችንና ሉዓላዊነታችን ዋስትና ነው !"በሚል መሪ ቃል የሀገሪቱን ሰንደቅ -ዓላማ በልዩ ልዩ መረሀ-ግብሮች ከፍ አድርጎ በማውለብለብ በድምቀት ይከበራል ።
የዘንድሮው የሰንደቅ-ዓላማ ቀን አገራዊ የእርቀ ሰላምና የምክክር ውይይቶችን በሚያስቀጥል መልኩ በመላ ሀገራችን ተስቦ እንዲውል ይደረጋል ያሉት ዋና አፈ-ጉባኤዋ ሰንደቅ -ዓላማችን የብሄራዊ ጀግንነታችንና የህብረብሔራዊ አንድነታችን ሕያው ምስክር ነው ሲሉ በአንክሮ ገልጸዋል ።
አክለውም አፈ-ጉባኤዋ አትሌቶችና ወታደሮችን ጨምሮ ሁሉም ዜጋ በተገኙበት አካባቢና የሙያ መስክ ሁሉ ለሰንደቅ -ዓላማው ክብር የሚመጥን ሰራ ጡጥሰራ ይገባል ሲሉም አጽንኦት ሰጥተው አሳስበዋል።