"ብዙ ታሪክ፣ ቅርስ ፣ባህል ፣ የተፈጥሮ ስጦታዎች ፣አዕዋፍ ፣የዱር አራዊት እና ሊጎበኙ የሚችሉ ድንቅ ሁነቶች እንዳሉን ግምት ውስጥ በማስገባት ከኢኮኖሚው ዘርፍ ዋና ምሦሦዎች አንዱ የቱሪዝም ሴክተሩ ነው።

ዛሬ የተከፈተው ሀገር አቀፍ የቱሪዝም እና ሆስፒታሊቲ አውደ ርዕይ ጎብኚዎች ኢትዮጵያን ምቹ መዳረሻ የሚያደርጋትን በናሙና እንዲያዩ ዕድል ይሰጣል። ያለንን ዐቅም ለማውጣት፣ ኢትዮጵያን የብዙ ውበቶች እና ግኝቶች መዳረሻ አድርጎ ለማስተዋወቅ እና ለማገልገል ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሀገራችሁ ያላትን ሀብት ማየት፣ ማውጣት፣ ማስተዋወቅ እና ማገልገል ይጠበቅባችኋል።

"ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ/ር)

Share this Post