በሀገር አቀፉ የቀዳማይ ልጅነት እድገት ፕሮግራም የልምድ ልውውጥ በትምህርት ቤቶች ሪፎርም እና በመጫዎቻ ስፍራዎች ግንባታ ዙሪያ ያተኮሩ የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብሮች ተካሄዱ

ከተለያዩ ክልሎች ለተወጣጡ ተሳታፊዎች ፕሮግራሙ ከጅማሬው አንስቶ አሁን እስከደረሰበት ደረጃ የነበረውን ሂደት ያብራሩት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የስራ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ መርሃ ግብሩ ወደ ተግባር ከመግባቱ በፊት ሰፊ የጥናት እና ተጠቃሚዎችን የመለየት ስራ መሰራቱን ተናግረዋል።

በዚህም 1.3 ሚሊዮን ከ 0-6 አመት ሕጻናትን በ ECD ፕሮግራም የተለያዪ ሥራወችን በመሥራት ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሠራ እንደሆነ እንዲሑም 330 000 ከድሕነት ወለል በታች የሚኖሩ እናቶችን በፕሮግራሙ ተጠቃሚ ማድረግ የሚያሥችል ሥራ ታቅዶ ሥራ ተጀምሯል።

በፕሮግራሙ ስድስት ኢኒሼቲቮች ተለይተው በእነሱ ላይ መስራት መጀመሩ የተገለጸ ሲሆን ከኢኒሼቲቮቹ ሁለቱ በሆኑት የትምህርት ቤቶች ሪፎርም እና የመጫዎቻ ስፍራዎች ግንባታ ረገድ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸው ተገልጿል።

በቀጣይ ሶስት አመታት 12ሺ የመጫወቻ ስፍራዎችን በከተማዋ ለመገንባት የታቀደ ሲሆን የመጫዎቻ ስፍራዎቹ በመኖሪያ መንደሮች፣ በፓርኮች ውስጥ ፣ በመንገዶች ላይ እና በተቋማት እና ድርጅቶች ውስጥ እንደሚገነቡ ተገልጿል።

1ሺ 59 የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶችን በማሻሻል ህጻናትን እያጫወቱ ለማስተማር ምቹ እንዲሆኑ ለማስቻል ታቅዶ እየተሰራ ሲሆን መምህራንን የማሰልጠን ፣ ሞዴል ትምህርት ቤቶችን የመፍጥር፣ የትምህርት ቤት ሱፐርቫይዘሮች እና ርዕሳነ መምህራንን ማሰልጠን መማሪያ ክፍሎችን የማሻሻል ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።

የምርሞር እና ስርጸት ስራም ትኩረት የሚሰጠው መሆኑ ተገልጿል።

Share this Post