ከሻንጋይ ጉብኝት በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቻይና ሲዥዋን ግዛት የምትገኘውን አረጓንዴዋን የቼንግዱ ከተማ ጎብኝተዋል::

ከቤጂንግ እና ሻንጋይ በመቀጠል ሶስተኛዋ ትልቅ ከተማ እንደመሆኗ ቼንግዱ ከኢትዮጵያ ጋር በብዙ መንገድ ቁርኝት ፈጥራለች:: ከነዚህም መካከል የቀጥታ የአየር ትራንስፖርት፣ የትምህርት፣የህክምና ትብብሮች እና የንግድ ግንኙነቶች ተጠቃሽ ናቸው::

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በቼንግዱ ቆይታቸው የግዙፍ ፓንዳ ማራቢያ /Giant Panda Base/ የጥናት ማእከልን እና የቲያንፉ የግብርና ኤክስፖ ፓርክን ጎብኝተዋል::

በሲዥዋን ግዛት የቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲ ኃላፊ ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር በተደረገላቸው የምሳ ግብዣ ወቅትም ትብብርን ለማጠናከር የሚያስችል አቅም ባላቸው መስኮች ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል::

#PMOEthiopia

Share this Post