ጳጉሜን-2 የመሥዋትነትን ቀን ምክንያት በማድረግ የደም ልገሳ መርሃ-ግብር በመዲናችን፣

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ እና የህብረተሰብ ተሳትፎ እና በጎ ፍቃድ ኮሚሽን በጋራ ባዘጋጁት በዚህ ፕሮግራም፣ የደም ልገሳ መርሃ ግብር በመከናወን ላይ ዬገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዮሀንስ ጫላ በመርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉትጠመልዕክት ከሰጦታዎች ሁሉ ስጦታ ደም መለገስ ሲሆን ይህንንም ተግባር ለመፈፀም ለተሳተፉው በጎ-ፍቃደኞች ምስጋና አቅርበዋል።

ሀገር ከፍ ብላ እንድትቆም የህይወት እና የአካል መሰዋትነት ለከፈሉ ወገኖቻችን በዚህ የተከበረ ተግባር አስበናቸው መዋላችን ለጀግኞቻችን አይበዛቢቸውም ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎፍቃድ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አብረሃም ታደሰ በበኩላቸው በየደረጃው መሰዋትነት እየከፈሉ ለሚገኙ ጀግኞቻችን እና የሀገር ባለውለታ ዜጎች ይህንን ቀን ለነሱ ክብር ለማድረግ እና በተለያዩ የበጎነት ተግባራትን መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

በመሥዋዕትነት የፀናች ሃገር

Share this Post