ከንቲባ ዶ/ር አዳነች አቤቤ አሜሪካ ጆርጂያ ግዛት ከሚገኘው ትሪኒቲ ኢንተርናሽናል አምባሳደርስ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ እና የጆርጂያ ግዛት የክብር ዜግነት ሽልማትን ተቀብለዋል።

ከንቲባ ዶ/ር አዳነች አቤቤ ለሕዝብ ተጠቃሚነት እና ለሰላም ላበረከቱት ታላቅ አስተዋፅዖ ፣ ያሳዩት በሳል እና ምሳሌያዊ አመራር በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚገኙ መሪዎች ምሳሌ የሚሆንና መነሳሳት የሚፈጥር በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው ይህንን Doctorate of Philosophy እንዳበረከተላቸው የትሪኒቲ ኢንተርናሽናል አምባሳደሪስ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ዶ/ር ዣክሊን ሞሀየር ገልፀዋል::

በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ነዋሪዎችን ህይወት ለመቀየር እና የነዋሪዎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከንቲባ ዶ/ር አዳነች አቤቤ ላሳዩት ቁርጠኝነት እና ለሌሎች ሃገራት መሪዎች አርአያ የሚሆን ስራ በመስራታቸው የጆርጂያ ግዛት የክብር ዜግነት ሽልማት እንደተበረከተላቸው የግዛቱ ሴናተር ጋይል ዴቨንፓርት በመድረኩ ላይ ተናግረዋል::

በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ ዶ/ር አዳነች አቤቤ ለዚህ ስኬት የበኩላቸውን አስተዋፅዖ ላበረከቱ አካላት በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል::

https://www.prweb.com/.../her-excellency-dr-adanech...

Share this Post