20
Nov
2023
ዛሬ የከተማችን የመኖሪያ ቤቶችን በመገንባት ለህብረተሰቡ በማቅረብ ላይ የሚገኘው ኖህ ሪል ስቴት የገነባቸው 754 መኖሪያ ቤቶች ተመርቀዋል።
ባለፉት 5 የለውጥ ዓመታት የተገነቡ 5000 ቤቶችን ጨምሮ እስከአሁን ከ8600 በላይ ቤቶችን ገንብቶ ለነዋሪዎች ያስተላለፈ ሲሆን፣ ግንባታቸው በመጠናቅቅ ላይ ያሉ ቤቶች በጥራት መገንባታቸውን እና የበርካታ ነዋሪዎችን የቤት ችግር የሚቀርፉ መሆናቸውን በጉብኝታችን ወቅት ተመልክተናል።
ለከተማችን ዕድገትና ለህዝባችን ፋይዳ ያላቸው በመሆኑ በመኖሪያ ቤት ላይ ለተሰማሩ ኩባንያዎች የከተማ አስተዳደራችን ድጋፍ ማድረጉን ይቀጥላል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ