ራዕይ የወለደው ለሚ እንጀራ ፋብሪካ

በቀን 288 ሺህ እንጀራ የሚጋገርበት እና እንጀራን ኢንዱስትሪያላይዝ በማድረግ በሃገራችን የመጀመሪያ የሆነው ለሚ እንጀራ ማዕከል፣ የእናቶችን ድካም የሚያቀልና እንጀራን ከፍ ባለ ደረጃ ማምረት የሚያስችል ነው።

የእንጀራ ማዕከሉ ከ2000 እናቶች በተጨማሪ በተለያዩ የስራ መስኮች ለ1000 ነዋሪዎች በጠቅላላው 3000 ለሚሆኑ ወገኖች የስራ እድል የፈጠረም ነው።

ለእንጀራ ፋብሪካው የተሻለ የገበያ ትስስር ለመፍጠር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቅርቡ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ጋር በመሆን የእንጀራ ፋብሪካውን መጎብኘታቸው ይታወሳል።

ዶ/ር ሳሙኤል በጉብኝታቸው ወቅት ከለሚ እንጀራ ፋብሪካ ጋር የተሻለ የገበያ ትስስር ለመፍጠር እና ፋብሪካው በቋሚነት ንፁህና ጥራት ያለው እንጀራ እያመረተ በመሆኑ በቀጣይ በቅርበት አብሮ ለመስራት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያለውን ተነሳሽነት ገልፀዋል።

የእንጀራ ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ማምረት እንዲችል በዛሬው እለት በፋብሪካው ለሚሰሩ እናቶች ለምርት እና ግብዓት ማመላለሻ የሚውል የተሽከርካሪ እገዛ የከተማዋን ራዕይ በሚጋሩ ባለ ሀብቶች ተደርጎለታል።

ባለሀብቱ አቶ በላይነህ ክንዴ ሶስት መለስተኛ ተሽከርካሪዎችን በፋብሪካው ለሚሰሩ እናቶች በስጦታ ያበረከቱ ሲሆን ከንቲባ አዳነች አቤቤም በከተማ አስተዳደሩ ስም አመስግነዋል።።

Share this Post