"ቴክኖሎጂው የመንግስትና የህዝብ ሃብትን በመመዝገብ በአግባቡ ለመጠቀም እና የሃብት ብክነትን ለመቀነስ የሚያስችል ነው።" ከንቲባ አዳነች አቤቤ

 

----------

የመንግስትን ንብረት በአንድ ማዕከል ማስተዳደር የሚያስችል ዘመናዊ ቴክኖሎጂ (Soft Ware) በይፋ ተመረቀ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን የመንግስትን ንብረት በአንድ ማዕከል ማስተዳደር የሚያስችል ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ዛሬ ይፋ አድርጓል።

ቴክኖሎጂው በ20 ተቋማት ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን እስካሁን ግምታዊ ዋጋቸው ከ1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ የሆኑ 455 የመንግስት ህንፃዎች እና 29 ሽህ 462 የመንግስት ንብረቶችን መመዝገብ መቻሉንም ባለስልጣኑ አስታውቋል።

ቴክኖሎጂውን መርቀው ስራ ያስጀመሩት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ቴክኖሎጂው የመንግስትና የህዝብ ሃብትን በመመዝገብ በአግባቡ ለመጠቀም እና በማስተዳደር የሃብት ብክነትን ለመቀነስ የሚያስችል ነው ብለዋል።

በቀጣይም በሞያው የሰለጠኑ ባለሙያዎችን በመመደብ በ668 የመንግስት ተቋማት ተግባራዊ ይደረጋልም ብለዋል።

ከንቲባ አዳነች አክለውም፣ ቴክኖሎጂው በሁሉም ተቋማት መተግበር ሲጀመርም የሐብት መቆጣጠር አቅማችንን ከፍ በማድረግ ብክነትን፣ ሌብነት እና ሌሎች ብልሹ አሰራሮችን ለመቅረፍ የሚያስችል መሆኑንም ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ የመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ የሱፍ ኢብራሂም በበኩላቸው የንብረት አስተዳደር ስርዓትን ለማሻሻል እና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን ገልፀው የለማው ቴክኖሎጂ የመንግስት ህንፃዎች አና ቋሚ ንብረቶችን ለታለመላቸው ዓላማ ለማዋል እንደሚያግዝ ገልፀዋል።

ቴክኖሎጂው በራስ አቅም የለማ በመሆኑ ምክኒያት መንግስትን 31 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ያዳነ መሆኑንም አቶ የሱፍ ተናግረዋል።

ለበለጠ መረጃ፦

👉 YouTube https://www.youtube.com/channel/UCagI4q5d_EtvTsajRXWnFjA

👉 Tik Tok https://www.tiktok.

👉 Telegram https://t.me/AAcommu

👉 Facebook https://www.facebook.com

👉 Website https://cityaddisababa.gov.et/

Share this Post