09
Dec
2023
በጅግጅጋ በድምቀት እየተከበረ ለሚገኘው 18ኛዉ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን እንኳን በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን!
ይህ ዕለት በብዝሀነት ውስጥ አንድነት የሚደምቅበት፣ ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ያስተሳሰረን ህዝቦች በድምቀት በጋራ የምናከብርው፣ በልዩነቶች ውስጥ ያለው አንድነት ጎልቶ የሚታይበት ፣ ኢትዮጵያን ለማበልጸግ የሰነቅነውን ታላቅ ራዕይ ዕውን ለማድረግ የገባነውን ቃል ኪዳን የምናድስበት ቀን ነው።
ኢትዮጵያዊነት አንድ ዓይነትነት አይደለም፤ ኢትዮጵያዊነት መለያየትም አይደለም፤ ኢትዮጵያውያን ከሚለያዩን ጉዳዮች ይልቅ በአንድነት ያጋመዱን ጉዳዮች ይበዛሉ። ኢትዮጵያዊነት መጠሪያችን ብቻ ሳይሆን፣ ማንነታችንም ነው።
መልካም በዓል ይሁንልን
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ