"የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የከተማችንን ሁሉን አቀፍ የልማት እንቅስቃሴ፣ ዓለም አቀፍ የስበት እንዲሁም የነዋሪዎቿን አዳጊ የመረጃ ፍላጎት ማዕከል አድርጎ ይሰራል" ወ/ሮ እናትአለዓም መለሰ

----------

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ለማህበራዊ ሚዲያው የሀሳብ አመንጪዎች እና በከተማ አስተዳደሩ የኮሙኒኬሽን ቢሮ መዋቅር ውስጥ ለሚያገለግሉ የዲጂታል ሚዲያ አካላት የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመግታት የሚረዱ ሙያዊ ክህሎቶች እና ለዘላቂ የአገር ግንባታ የሚበጅ ሚዛናዊ የመረጃ ስርጭት ዙርያ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ስልጠና ሰቷል።

የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ እናትዓለም በስልጠና መርሃ-ግብሩ ማጠቃለያ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ዜጎች ከሀሰተኛና አፍራሽ መረጃዎች ተጠብቀው ለሀገር ግንባታ የሚበጅ ሚዛናዊ አመለካከት እንዲይዙ ለማስቻል የማህበራዊ ሚዲያው የሀሳብ አፍላቂዎች ሚናቸው የጎላ ነው ብለዋል።

በዲጂታል ሚዲያው ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ባለሞያዎች እና ልዩ ልዩ አካላት ከፍተኛ አገራዊ ኃላፊነት እንዳለባቸው የገለፁት ወ/ሮ እናትዓለም፣ ከተማችን አዲስ አበባ አሁን ላይ የደረሰችበትን የልማት፣ የመልካም አስተዳደር፣ የፕሮጀክት አፈፃፀምና የሰው ተኮር ተግባራት አፈፃፀም የሚመጥን የማህበራዊ ሚዲያ ስራ እንደሚጠበቅ ገልፀው ለዚም ይህ ስልጠና ከፍተኛ የአቅም ግንባታ መሆኑን አስረድተዋል።

መዲናችን አዲስ አበባ በዘላቂነት የነዋሪውን ህይወት የሚቀይሩ ስራዎች እየሰራች ሲሆን ይህንን በሚመጥን እና የነዋሪዎቿን ህብረ- ብሔራዊ አንድነት በሚያጠናክር ሁኔታ ፍጹም ሚዛናዊ የመረጃ ስርጭት አግባብን ልትከተሉ ይገባልም ሲሉ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

የቢሮው ምክትል ኃላፊና የዲጂታል ሚዲያ ዘርፍ ኃላፊ አቶ በትግሉ ኪታባ በበኩላቸው ከሀሰተኛ መረጃ እራስንም ማህበረሰባችንንም ለመታደግ ወቅቱን የሚመጠን ስልጠና እና ተከታታይ የአቅም ግንባታ በማስፉለጉ ይህ መርሃ-ግብር ተዘጋጅቷል ያሉ ሲሆን ቢሮው ይህንኑ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

ለተጨማሪ መረጃ፦

👉 YouTube https://www.youtube.com/channel/UCagI4q5d_EtvTsajRXWnFjA

👉 Tik Tok https://www.tiktok.

👉 Telegram https://t.me/AAcommu

👉 Facebook https://www.facebook.com

👉 Website https://cityaddisababa.gov.et/

Share this Post