የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውሀና ፍሳሽ ባለስልጣን የአገልግሎት አሰጣጡን ዲጂታላይዝድ ለማድረግ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር መስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።

 

በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የከንቲባ ፅ/ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ጥላሁን ወርቁ ስምምነቱ የውሃና ፍሳሽ መሰረተ ልማት መረጃዎችን በዘመናዊ መንገድ አደራጅቶ ለመያዝ፣ ዲጂታላይዝድ የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት ብክነትን በማስቀረት አገልግሎቱን ፈጣንና ቀልጣፋ ማድረግ የሚያስችል ስማርት የማኔጅመንት ስርዓት ለመዘርጋት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የያዘውን ዕቅድ ለማስካት የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ የውሃ አገልግሎትን በዘመናዊ መንገድ ለማስተዳደር የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት የጀመረውን ስራ አድንቀው ፕሮጀክቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ወደ ስራ እንዲገባ ለማድረግ እንደሚሰሩም ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ዘሪሁን አባተ በበኩላቸው ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የውሃና ፍሳሽ ደንበኞቹን በተመለከተ የጠራ፣ የተረጋገጠ፣ ወቅታዊነትን የተላበሰና የተቀናጀ መረጃ ይኖረዋል ብለዋል።

ለተጨማሪ መረጃ፦

👉 YouTube https://www.youtube.com/channel/UCagI4q5d_EtvTsajRXWnFjA

👉 Tik Tok https://vm.tiktok.com/ZM6jGNeFE/

👉 Telegram https://t.me/AAcommu

👉 Facebook https://www.facebook.com

👉 Website https://cityaddisababa.gov.et/

Share this Post