15
Dec
2023
------------
የአድዋ ዜሮ ኪሎሜትር ሙዚየም ፕሮጀክት በዛሬው እለት በአገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ የሚዲያ አካላት ተጎብኝቷል።
የአዲስ አበባ ከንቲባ ፅ/ቤት እና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ጥላሁን ወርቁ ለጎብኚዎቹ በሰጡት ማብራሪያ የአድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚየም ፕሮጀክት የኢትዮጵያ አንድነት መገለጫ ምሶሶ ነው ያሉ ሲሆን አዲስ አበባ የአድዋን ሙዚየም ታሪኩን በሚመጥን ሁኔታ የታሪክ አሻራ እያኖረች ነው ብለዋል።
ከ185 በላይ የሚሆኑ የአገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ የሚዲያዎች አመራሮች፣ ጋዜጠኞች ሪፖርተሮች እና የኮሙኒኬሽን ባለሞያዎች የአድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚየም የደረሰበትን አሁናዊ የግንባታ ደረጃ የጎበኙ ሲሆን ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ዙሪያ ጭምር ሰፊ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።
ለተጨማሪ መረጃ፦
👉 YouTube https://www.youtube.com/channel/UCagI4q5d_EtvTsajRXWnFjA
👉 Tik Tok https://vm.tiktok.com/ZM6jGNeFE/
👉 Telegram https://t.me/AAcommu
👉 Facebook https://www.facebook.com
👉 Website https://cityaddisababa.gov.et/