18
Dec
2023
በጉብኝታቸውም ዘመናዊ የከተማ መዋቅራዊ ፕላን እና አተገባበር፣ በመሰረተ ልማት ቅንጅትና ግንባታ ፣ በመሬት አጠቃቀምና አስተዳደር እንዲሁም ዘመናዊ ከተማ መገንባት በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ከሻንጋይ ከተማ ፕላን እና የተፈጥሮ ሃብት ቢሮ አመራሮች ጋር ፍሬያማ ውይይት እንዲሁም ጉብኝት አድርገዋል::
የቻይና የንግድ ማዕከል የሆነችው የሻንጋይ ከተማ በምትታወቅበት ዲጂታላይዝድ አገልግሎቶች እና በስማርት ሲቲ ግንባታ ሂደት ለሃገራችን ከተሞች ልምድ በምታጋራበት እና አብሮ መስራት በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል::
በጉብኝቱ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ም/ከንቲባ ጃንጥራር አባይ ፣ የብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ኃላፊ ሞገስ ባልቻ ፣ የባህርዳር ከተማ ከንቲባ ጎሹ እንዳለማው፣ የሃዋሳ ከተማ ከንቲባ መኩሪያ መርሻዬ እንዲሁም ሌሎች የፌደራልና የከተሞች ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል::
ለተጨማሪ መረጃ፦
👉 YouTube https://www.youtube.com/channel/UCagI4q5d_EtvTsajRXWnFjA
Tik Tok https://vm.tiktok.com/ZM6jGNeFE/
👉 Telegram https://t.me/AAcommu
👉 Facebook https://www.facebook.com
👉 Website https://cityaddisababa.gov.et/