ሁለቱ ከንቲባዎች ባደረጉት ውይይት ለሃምሳ አመታት የዘለቀው የኢትዮ-ቻይና ዲፕሎማሲያዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ወደ በማንኛውም ሁኔታ ፀንቶ የሚቆይ ስትራቴጂያዊ ግንኙነት (All-weather Strategic Cooperation Partnership) ማደጉ በአዲስአበባ እና በሻንጋይ ከተሞች መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እና በጋራ ጉዳዮች ላይ ተቀራርቦ ለመስራት ከቀድሞ ይበልጥ ምቹ ሁኔታ የፈጠረ መሆኑን አንስተዋል::
አክለውም ከንቲባ አዳነች የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር በፋይናንስ ፣ በንግድ ፣ በቴክኖሎጂ እና በማኑፋክቸርንግ ዘርፍ ባስመዘገበችው አስደናቂ ልማት ከምትታወቀው ከሻንጋይ ከተማ ጋር በጋራ ጉዳዮች ላይ ለመስራት እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚሰሩ ተናግረዋል::
ከንቲባ ጎንግ ዜንግ በበኩላቸው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ፣ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ማዕከል እንዲሁም ፈጣን ለውጥ እያስመዘገበች ካለችው እና የአፍሪካ መግቢያ በር ከሆነችው አዲስ አበባ ከተማ ጋር ተቀራርቦ መስራት የሁለቱን ከተሞች የጋራ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑን አንስተዋል::
በቀጣይም የእህትማማች ግንኙነት በመመስረት በንግድ ፣ በቱሪዝም ፣ በኢንቨስትመንት ፣ በቴክኖሎጂ ፣ በአቅም ግንባታ፣ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በማጠናከር እንዲሁም በሌሎች ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ የሁለቱም ከተሞች ከንቲባዎች ባደረጉት ውይይት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል::
ለተጨማሪ መረጃ፦
👉 YouTube https://www.youtube.com/channel/UCagI4q5d_EtvTsajRXWnFjA
👉 Tik Tok https://vm.tiktok.com/ZM6jGNeFE/
👉 Telegram https://t.me/AAcommu
👉 Facebook https://www.facebook.com
👉 Website https://cityaddisababa.gov.et